ህግ እና ደንቦች

ለወላጆችና ለአስጠኚዎች የሥራ መመሪያዎችን ይመለከታል።

ለወላጆች

1

ወላጆች በGoogle Form፣ Telegram ወይም በስልክ ይመዝገቡ

2

የልጆችዎን ፍላጎት ፡ የልጅዎን እድሜ፣ ደረጃ፣ የመማር ፍላጎት በትክክል ያስቀምጡ

3

አስጠኚዎች ስራ ከመጀመራቸዉ በፊት መስማማትዎን ያረጋግጡ።

4

የመጀመሪያ ውይይት ከአስጠኚዎች ጋር ያድርጉ

5

የጥናት ቦታውን ንጽህና እና ደህንነት ያረጋገጡ

6

አስተያየትዎን ወይም ቅሬታዎን ያቅርቡ፤ ካስፈለገ አስጠኚ ወይም እቅድ እንቀይራለን

ለአስጠኚዎች

ጊዜ ማከበር እና ህጎችን መከተል

ወላጆች ማክብር እና በትህትና መስራት

ከወላጆች እና ከተማሪዎች አስተያየት መቀበል፤

ይነበብ ‼ ‼ ‼

ልጀን አደራ ቤት ለ ቤት አስጠኚ አገናኚ ድርጅት።

👋ሰላም እንዴት ናችሁ በድርጅታችን ሰም ሰላምታችን በያላችሁበት ይድረስ እያልን፤ ዛሬ ለተማሪ ወላጆች እና በአስጠኚነት በድርጅታችን ለተመደባችሁ ጎበዝ እና ታታሪ ለሆናችሁ አስጠኚዎቻችን በሙሉ በድርጅታችን ጸድቀው የወጡ መልዕክቶች ስላሉን እነሱን እናሳውቃለን በጥንቃቄ ይነበብ።

ይነበብ ‼ ‼ ‼

♨ሁላችሁም የድርጅታችን አባላት እንደምታውቁት ድርጅታችን ጎበዝ እና የሰለጠኑ አስጠኚዎችን በመቅጠር አንቱ የተባለ እና ለተማሪዎቻችን የነገ ስኬታቸው ላይ ለማድረስ ቀን ከሌት እየሰራ ይገኛል።

❎ታድያ ከትንሽ አመታት በፊት የተጀመረው የትምህር ስርዓት ተማሪዎቻችን እየፈተነ ተስፋ ወደማስቆረጡ ደርሶዓል።

✅ታድያ በዚህ ስዓት ሁላችንም የቤት ውስጥ የመማር ማስተማሩን ሂደት በማሻሻል የተማሪዎቻችን ተስፋ መልሰን የነገ ተሰፋቸውን የሚያዩበትን ፋኖስ እናበራለን።

ታድያ እሄ የሚሆነው በሚከተሉት ተግባራት ነው።

🔴 አስጠኚ ሆናችሁ ለተመደባችሁ የወጣ ተግባር፦

  • 🔺 አንዳንድ ምዕራፍ እንደጨረሳችሁ ሁልጊዜም የምዕራፉን ጠቅለል ያለ ሀሳብ የያዙ ጥያቄዎችን በማውጣት መፈተን።
  • 🔺 አንዱ ምዕራፍ እንዳለቀ ሁልጊዜም ተማሪው የምዕራፉን ጠቅለል ያለ ማብራሪያ እንዲያደርግ ማድረግ።
  • 🔺 ማጣቀሻ(አጋዥ) መጽሀፍትን ተጠቅመው እንዲሰሩ የሚያደርግ ጥያቄ በየቀኑ መስጠት።
  • 🔺 ክፋል ውስጥ የሚሰጣቸውን የቤት ስራ እና አሳይመንት ቅድሚያ እነሱ እንዲሞክሩ ማድረግ።
  • 🔺 በየቀኑ ምታጠኑትን በጥያቄ ማጠናከር።
  • 🔺 ሁሌም አስጠንታችሁ ሰትወጡ ለቀጣይ ቀን ሰርተው ሚጠብቋችሁ ጥያቄ መስጠት አለባችሁ።

🔵 ለተማሪ ወላጆች የወጣ መልዕክት፦

  • 🔹 ምቹ የሆነ(ፀጥ) ያለ የሚያጠኑበት ቦታ ማመቻቸት አለባችሁ።
  • 🔹 ከላይ እንደምሳሌ የተቀመጡት ተግባራት እየተተገበሩ መሆኑን ማረጋገጥ።
  • 🔹 ልጅዎ አስጠኚዎች ከመምጣታቸው በፊት የተሰጠውን የቤት ስራ እንዲሰራ ማድረግ።
  • 🔹 አስጠኚዎች በሚመጡበት ስዕት ልጅዎ ለማጥናት እንዲዘጋጅ ማድረግ።

📶እነዚህ ከብዙዎቹ ጥቂቶቹ ናቸው።

አንተም፣ አንችም እኔም የተማሪ ልጆቻችን ጉዳይ ይመለከተኛል፤ የነሱ ጉዳይ የኔም ጉዳይ ነው በሚል መርህ የተሻለን ነገ እንፍጠር ይላል ድርጅታችን ልጀን አደራ ቤት ለ ቤት አስጠኚ አገናኚ ድርጅት።

ሀሳብ አስተያየት ካለ እንቀበላለን Inbox me 🙏🙏🙏